image
image
image
image
image

‎"የጉባ ብስራቶች የወል ትርክት ትዕምርቶች!"

ጥር 7-2018, 2018
‎የልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 6 ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት “የጉባ ብስራቶች የወል ትርክት ትዕምርቶች!" በሚል መሪ ቃል ደማቅ የኪነ-ጥበብ ምሽት አካሂዷል። ‎ ‎በመድረኩ የተገኙት የአዲስ አበባ አስተዳደር የመንግስት ግዢና ንብረት ማስወገድ ም/ሥራ አስኪያጅ አቶ ምስጋን ከበደ እንደገለጹት የኪነ-ጥበብ ስራዎች በማህበረሰቡ ዘንድ የወል ትርክት፣ሰላም አንድነትንና ልማትን ለማስረፅ ትልቅ አቅም እንዳላቸው ገልፀው ብልፅግና ፓርቲ መነሻው የሀሳብ ልዕልና መሆኑንና ሀሳብ በጥበብ ሊታሽ እንደሚገባው ተናግረዋል ። ‎ ‎የልደታ ክ/ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አሰፋ ቶላ ብልፅግና ፓርቲ ከለውጡ ማግስት በሰራቸው በርካታ ሰው ተኮር ስራዎች የሚታይ የሚጨበጥ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን ጠቅሰው ፓርቲው ሀገሪቱን በአፍሪካ ብሎም በአለም የብልፅግና ተምሳሌት ለማድረግ እየሰራ በሚገኘው ስራ ነጠላ ትርክትን በማስወገድ የወል ገዢ ትርክትን በማስረፅ የተጀመረዉን ልማት ለማስቀጠል መስራት ከሁላችን ይጠበቃል ሲሉ ገልፀዋል። ‎ ‎ የልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 6 ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ዮዲት ሰለሞን ሀገሪቱ ከለውጡ በፊት በተለያዩ ስርዓቶች የተለያዩ ስብራቶች ሲያጋጥሟት መቆየቱን ጠቅሰዉ ይሁንና ከለውጡ ማግስት ጀምሮ ብልፅግና ፓርቲ የመደመር ዕሳቤን ይዞ በመነሳት ሁሉንም በእኩል በማሳተፍ ሁለንተናዊ ዉጤት እያመጣ እንደሚገኝና ለውጡን ለማስቀል የኪነ-ጥበብ ስራዎች ፋይዳቸው ትልቅ መሆኑን ተናግረዋል። በፕሮግራሙ የሙዚቃ፣ውዝዋዜ እንዲሁም ፓርቲው ከገዢ ትርክትን ለማስረጽ እየሰራ ያለውንና የሚገልጽ ግጥምና መጣጥፍ ቀርቧል። ‎#lideta_wereda_6_prosperity_party

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች