image
image
image
image
image

በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የሴክተር አባላት ህብረት "በተናበበ ስምሪት፣ በላቀ ትጋት፣ አዲስ አበባን የብልጽግና ተምሳሌት" በሚል መሪ ቃል የ2018 ዓ.ም 2ኛ ሩብ ዓመት ኮንፍረንስ ተካሄደ።

ታህሳስ 16, 2018
የልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ዮዲት ሰለሞን እንደገለፁት ከዝግጅት ምእራፍ ጀምሮ በስድስት ወር ውስጥ በርካታ ስራዎች የተከናወኑ እና ውጤት ተኮር አፈፃፀም መኖሩን የገለፁት ሲሆን ጠንካራ ህብረት መገንባት እና በስሩ በሚገኙ ቤተሰቦችን የአቅም ግንባታ እና መዋቅሩን በማጠናከር በአፈፃፀም ሂደት የታዩ ጥንካሬዎች በማጠናከርና የታዩ ውስንነቶች በፍጥነት በማረም በቀጣይ የስራ ትኩረት ተደርጎ በመስራት የተመዘገቡ መልካም ውጤቶችን በማሳለጥ እና አጠናክሮ በማስፋፋት የሁሉም አባላት የሚጠበቅባቸውን ሚና ሊወጡ እንደሚገባ ገልፀዋል። በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 6 ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ምክትል ፓርቲ ኃላፊ እና የፓለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ዳምጠው ወንታሞ በበኩላቸው እንደገለፁት የፓርቲያችን አባለት በትክክል የመደመርን እሳቤ በማስጨበጥ እና በመረዳት በፓርቲው ስራዎችና በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ያለውን ተሳትፎ ማሳደግ የኮንፈረንሱ ዋነኛ ግብ መሆኑን ገልፀው፣በአደረጃጀቱ ውስጥ ያለውን ድርሻ በማጠናከር ለተሟላ ስኬት መትጋት እንዳለባቸው ገልጿል። በኮንፍረንሱም በህብረት አመራሮች የ2ኛ ሩብ አመት ስራ አፈፃፀም ሪፖርት፣ የኢንስፔክሽን ስነ-ምግባር ኮምሽን የ2ኛ ሩብ ዓመቱ ሪፖርት ለአባላት ቀርቦ በጥልቀት ውይይት ተደርገዋል። ጠንካራ የፓርቲ ተቋም በመፍጠር ከተማችን የብልፅግና ተምሳሌት ለማድረግ እና የሀሳብ የበላይነት በመያዝ እንድሁም የውል እውነቶች በማስረፅ ከቃል በላይ በተግባር የተረጋገጠበት ዓመት እንዲሆን መስራት እንደሚገባ ተገልፆል። በመጨረሻም በመደመር እይታ የአባላትን ንቁ ተሳትፎ ማረጋገጥ በሚቻልባቸው ስልቶች ላይ ጥልቅ ውይይት የተደረገ ሲሆን፣ከአባላቱ የቀረቡ የተለያዩ የትኩረት አቅጣጫዎችና አጀንዳዎች በተሳታፊዎች ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸው በሙሉ ድምፅ በማፅደቅ ኮንፈረንሱ ተጠናቋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች