የልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 06 ብልጽግና ፓርቲ ዋና ዋና ተግባራት

  1. በቴክኖሎጂ የታገዘ የክትትልና ድጋፍ ሥርዓት በመዘርጋት የፓርቲና የመንግሥት ዕቅዶች በውጤታማነት እንዲፈጸሙ ማድረግ
  2. በቴክኖሎጂ የታገዘ የመረጃና ዶኩመንቴሽን ሥርዓት መዘርጋትና በቀጣይነት ማሻሻል
  3. ወቅቱን የዋጀ ሐሳብ በማመንጨት፣ በተከታታይ የአቅም ግንባታ፣ በየጊዜው የሚጋጥሙ ስህተቶችን በማረምና ስኬቶችን በማስቀጠል የፓርቲውን ቀጣይነት ማረጋገጥ
  4. በአመራሩ፣ በአመራሩና በአባሉ፣ በትውልዶች መካከል ወንድማማችነትና እህትማማችነትን ማጎልበት
  5. ወቅቱን የዋጀ ሐሳብ በማመንጨት፣ ስህተቶችን በማረም፣ ስኬቶችን በማስቀጠል የፓርቲውን የመፈጸም አቅም ማሳደግ
  6. በህብረ-ብሄራዊ ፌደራሊዝም፣ በወልና በነጠላ እዉነት ላይ ቀጣይነት ያለው ውይይት ማድረግ
  7. ትምህርት ተቋማት ብቁ ዜጋ ማፍራት እንዲችሉና ምሁራን ለሀገር ግንባታ ስኬታማነት የበኩላቸዉን ሚና እንዲወጡ ማስቻል
  8. በተደራጀ የሕዝብ ተሳትፎና በውጤታማ የአሰራር ሥርዓት የህዝብ አመኔታና እርካታ ማሳደግ
  9. በግልፅ የተልዕኮ ስኬት ላይ የተመሰረተ የምደባ ስርዓት በመዘርጋት እና የምዘናና እውቅና ስርዓት እውን በማድረግ የፓርቲ ተቋማዊ ጥንካሬ ማሳደግ
  10. የፓርቲውን አደረጃጀትና አሰራሮች በማዘመን የፓርቲውን ተቋማዊ ጥንካሬ ማሳደግ
  11. በየደረጃው ያለው አስተባባሪና አመራር ኮሚቴ፣ የአደረጃጀቶች አመራሮች፣ መሰረታዊ ድርጅት፣ ሕዋስ ቋሚ ግንኙነት ጊዜያቸውን ጠብቀው ግምገማና ውይይት ማካሄዳቸውን ማረጋገጥ
  12. የፓርቲ አደረጃጀቶች፣ አመራሮች፣ አባላት፣ መረጃ በቴክኖሎጂ የተደገፈ፣ የሚተዳደር እንዲሆን ማድረግ
  13. በፓርቲው መተዳደሪያ ደንብና አሠራር መሰረት ነባሩን አመራርና አባሉን በማጥራት አዳዲስ አባላት ምልመላ በማድረግ የፓርቲውን መሠረት ማስፋት
  14. በመላ አባላቱ ዘንድ ተቀባይነት ያለው በየደረጃው የውስጥ ምርጫ በማካሔድ የፓርቲውን ዴሞክራሲያዊነትና አመራር ማረጋገጥ
  15. ጥራትና ብቃት ያላቸውን ዕጩ ለሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ በማዘጋጀት የፓርቲውን ተወዳዳሪነት ማሳደግ
  16. የከተማውን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እቅዶችን በብቃት ማቀድና መፈፀምየሚችል አመራር በየደረጃው ማፍራትና ማብቃት
  17. ከፖለቲካ ፓርቲዎችና ሲቪል ማህበራት ጋር መርህን የተከተለ ግንኙነት በማጠናከርና ለሀገር ግንባታ ያላቸውን አስተዋፆ በማሳደግ ሀገራዊና ከተማዊ መግባባት ማጠናከር
  18. ከሲቪል ማህበራት ጋር ግልፅና ተከታታይ የግንኙነት ስርዓት በመዘርጋት ለዲሞክራሲ ባህል ግንባታና ለኢኮኖሚ እድገት ያላቸውን አስተዋፆ አሟጦ መጠቀም
  19. ለመብቱ የሚታገልና ግዴታውን የሚወጣ የሰለጠነ ማህበረሰብ ለመፍጠር የሚያግዙ የዴሞክራሲ ተቋማትን መገንባት
  20. የሴቶችና ወጣቶች ሊግ አደረጃጀቶችን በማጠናከር ፖለቲካዊ ተሳትፎና ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ አበርክቶና ተጠቃሚነታቸውን ማረጋገጥ
  21. የሴቶች የፖለቲካ ተሳትፎ ማሳደግ
  22. የሴቶች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ማሳደግ
  23. የወጣቶች ሊግ አደረጃጀቶችን በማጠናከር የወጣቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ
  24. የመደመር ትውልድ መገንባት
  25. በ2018 እና በ2023 ለሚካሄደው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ በቂ ዝግጅት ማካሄድ
  26. አመራሩ በሚያመነጨው ሀሳብ አባሉና ሌሎች ሰዎች እንዲገዙትና አምነው በፍላጎት እንዲደግፉት መግባባት መፍጠር
  27. የብዙሃን መገናኛ ዘዴዎች ሽፋን አሟጦ መጠቀም
  28. በፓርቲ እሳቤዎችንና ስኬቶች ላይ ብቃት ያለው የተግባቦት ሥራ በመሥራት፣ የጋራ ማንነትና የወል እውነቶችን ለመገንባት የሚያግዙ ተቋማትንና ስርዓትን በማጠናከር የትርክት የበላይነት ማሳደግ
  29. ለአረጋውያን እና ለአቅመ ደካሞችን ቤት መገንባት ለተጠቃሚዎች እንዲተላለፍ ማድረግ
  30. የፓርቲው የንድፈ ሀሳብ መጽሔት ልሳነ ብልፅግና እንዲታተምና እንዲሰራጭ ማድረግ
  31. ለፋይናንስ ስራዎች የሚያገለግሉ ሰነዶችና ደረሰኞች እንዲታተሙ ማድረግ
  32. የፓርቲው ንብረት በአግባቡ ተመዝግቦ እንዲያዝ ማድረግ
  33. ገቢ እና ወጪ ዕቃዎች አሰራርን በተከተለ አግባብ እንዲፈጸም ማድረግ