image
image
image
image
image

የከተማ ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ በልደታ ክፍለ ከተማ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ምልከታ አደረገ ።

ሰኔ 10, 2018
በምልከታው ወቅት ምክር ቤቱ በክፍለ ከተማው የሚገኝው የአንድ ማዕከል አገልግሎትና ሌሎች የአገልግሎት ሰጪ ተቋማትን በጎብኘት ለሕዝብ የሚሰጠውን አገልግሎት ሂደት፣ ፍጥነት እና ጥራት ተመልክቷል። የምክር ቤቱ አባላት ለሕዝብ ቀልጣፋና ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠት የሚደረጉ ጥረቶችን በማጠናከር የአገልግሎት ተደራሽነትንና ውጤታማነትን የበለጠ ለማሻሻል የተሰራው ስራ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ተብሏል። የልደታ ክፍለ ከተማ በአንድ ማዕከል አገልግሎትና በተለያዩ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አማካኝነት የተገልጋዮችን ጥያቄና ፍላጎት በማዳመጥ ፈጣንና ቀልጣፋ ምላሽ እየሰጠ ነው በክፍለ ከተማው የተለያዩ አገልግሎቶችን ፈልገው የሚመጡ ተገልጋዮች በአንድ ማዕከል አገልግሎት ተደራሽ በሆነ ሁኔታ ጉዳያቸውን በማስፈጸም አገልግሎታቸውን አግኝተው እየተመለሱ መሆኑን ተገልፀዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ