image
image
image
image
image

"ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ሁሉን አቀፍ ለውጥ በሴቶች ተሳትፎ ይረጋገጣል" በሚል መሪ ቃል የሴቶች ቀን ( March 08)በልደታ ክፍለ ከተማ ሴቶችና ህፃናት ጽ/ቤት አስተባባሪነት በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል፡፡

የካቲት 28, 2017
በልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዘንድሮ በዓለም ለ114ኛ በሃገራችን ለ49ኛ ጊዜ እየተከበረ የሚገኘው ዓለማቀፉ የሴቶች ቀን "ፈጣን እና ሁሉን አቀፍ ለውጥ በሴቶች ተሳትፎ ይጋገጣል" በሚል ቃል የሴቶች ቀን ( March 08 ) በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል። የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አበባ እሸቴ እንደገለፁት ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ከኢትዮጵያ ሴቶች የትግል ታሪክ አንፃር ሴቶች ላይ ይደርሱ የነበሩ ፆታዊ ጭቆናዎች በማስቀረትና ከዚህ ቀደም የነበሩ የስርዓቱ ነፀብራቅ በሆኑ አባባሎችን በማስቀረት ሴቶች እኩል ተሳታፊና ተጠቃሚ የመሆን መብት እንዲከበር የተሰሩ ተግባራት ውጤት ማፍራቱን ገልፀዋል የልደታ ክፍለ ከተማ ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ፅ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሄለን መሀመድ በበኩላቸው የሴቶችን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተጠቃሚነትና ተሳታፊነት ለማሳደግ በርካታ ስራዎች መሠራቱን ገልፀው የሴቶች የማብቃትና የሴቶችን አደረጃጀቶችን በማጠናከርና ሁለንተናዊ አቅማቸውንና ተጠቃሚነታቸውን እንዲሁም ተሳትፏቸውን በማሳደግ በሁሉም ዘርፎች የራሳቸውን ሚና እንዲወጡ ለማድረግ ይገባል በማለት ገልፀዋል። በመድረኩም የሴቶችን ቀን በማስመልከት የተለያዩ መልዕክቶችንና ትዕይንቶች ማሳየት ተችሏል።

መልዕክትዎን ይላኩ