image
image
image
image
image

በልደታ ክ/ከተማ "ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ሁሉን አቀፍ ለውጥ በሴቶች ተሳትፎ ይረጋገጣል" በሚል መሪ ቃል ዓለም አቀፍ የሴት ቀን አስመልክቶ የፓናል ውይይት ተካሂዷል።

የካቲት 27, 2017
የፖናል ውይይቱን የልደታ ክ/ከተማ ሴትች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት አዘጋጅተውታል። የሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሄለን መሀመድ እንደተናገሩት ሴቶች እኩል ተጠቃሚነታቸውና መብታቸው እንዲከበርና በልማትና በመልካም አስተዳደር ስራዎች ያላቸውን አበርክቶ ተጠናክር እንዲቀጥል መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ብለው ሴቶች ተፈጥሯዊም ሆነ ሰው ሰራሽ ልዩነቶች ሳይገድቧቸው ለጋራ መብታቸው የሚያደርጉትን ትግል አጠናክረው እንዲቀጥሉም አሳስበዋል። ሴት ልጅ ለሚገጥሟት ችግሮች መፍትሄ የማታጣ የማስተዋል አቅምን የተቸራት ናት ያሉት ወ/ሮ ሄለን ይህንን አቅም በመጠቀምም ለሰላም መስፈን አስተዋፆ ማድረግ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል። የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ለሴቶች እኩልነትና መብት መከበር ከምንጊዜውም በላይ የድርሻቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ