የፖለቲካ ፕሮግራም

የብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካ ፕሮግራም ዋነኛ ዓላማ፡- ጠንካራና ቅቡልነት ያለው፣ የብሔር ማንነትን እና የሀገራዊ አንድነትን ሚዛን የጠበቀ ሀገረ-መንግስት መገንባት ነው።

ከጠንካራ ሀገረ-መንግስት ግንባታ አንፃር ፓርቲያችን ህዝብ ከቀጥተኛ የህልውና አደጋ ተጠብቆ የልማት፣ የእኩልነት እና የነፃነት ፍላጎቶቹ እንዲሟላለት የሚያስችል ነፃ፣ ገለልተኛና ብቃትን መሰረት ያደረገ ሀገራዊ ተቋማዊ አደረጃጀት መገንባት ያስፈልጋል ብሎ ያምናል።

የፖለቲካ ፕሮግራም ግቦች

  1. ጠንካራና ቅቡል ሀገረ መንግሥት በጽኑ መሠረት ላይ ለመገንባት የሚያስችል ሀገራዊ መግባባት መፍጠር
  2. በተቋማዊና ሕዝባዊ ባህል ላይ የቆመ የዴሞክራሲ ሥርዓት መገንባት
  3. ዘላቂና አዎንታዊ ሰላምን ማረጋገጥ